Thursday, June 22, 2017

Reflection and Addition to Ato. Henok Yeshitila's Article

አቶ ሄኖክ የሺጠላ Ethiopatriots ድህረ ገጽ ላይ የጻፈውን "ብርሃኑ ነጋ አርሾ በመስረቅ የሚስተካከለው የለም" በሚል አርስት የፃፈውን አጭር ፅሁፍ አንብቤ ስቸርስ መልስ ለመስጠት ተነሳሁ። ከሞላ ጎደል አቶ ሄኖክ ስለ ድክተር ብርሃኑ በተናገረው አስማማለው። ሆኖም ግን አንዳንድ ይበልጥ ብአብራራቸው ወይም አጎደለ ብዬ የሚለውን ሃሳብ በዚህ ፅሁን ለማከል አወዳለው።
በመጀመርያ ግንቦት ሰባት የተቁዋቁአመው በአማራ ደም ለመነገድ ነው ይላል አቶ ሄኖክ። እንዴታ። አቶ ተክለ ይሻው ለአቶ ኤፍሬም ማዴቦ ፅሁፍ መልስ በሰጡበት ጽሁፋቸው ላይ የብርሃኑ አና ግንቦት 7 ሰዎች ለአማራው ያላቸውን ቦታ በሚገባ አብራርተዋል። ይህም ግንቦቴዎች አማራውን የሚፈልጉት ለአጀባ አና ወንበር አስተካካይነት አንደሆነ ነው። ያ የነ ብርሃኑ አካሄድ ደግሞ አቶ ሃዕሌ ላረቦ አማራን በተመለከተ በፃፉት ጽውፋቸው ላይ አንደገለጹት የጥንታዊት  ኢትዮጵያ ነገስታት ያረጉ እንደነበረው ነው። ማለትም በአማራው መንገት ተራጊነት ስልጣን መቆናጠጥና የስልጣን ግባቸው ሲሳካ ያን ለዝያ ያበቃቸውን አማራውን ማግለል ብሎም መቸኮን። አነ Dr ብርሃኑ በቅንጅት  ጊዜ ሊያረጉ የሞከሩት ይሄንኑ ነበር። ብርሃኑ ነጋ አዲስ የፈጠረውን አና ከአዲስ አበባ አና ዲላ በስተቀር ቢሮ አንኩዋን ያልነበረውን ቀስተደመና የሚባል ድርጅቱን ይዞ የቅንጅት አባል በመሆን የአማራ ድርጅት ብሎ በሚፈርጀው መኢአድ ለአመታት ባዋቀራቸው ድርጅታዊ ተቁአማት ተጠቅሞ ስልጣን ልመ ጨብጥ ነበረ አላማው። ያም ማለት በቅንጅት ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ በአውሮፓ አና ሰሜን አሜርካ የነበሩ የቅንጅት ጽሕፈት ቤቶች አና ቻፕተሮች በሙሉ ማለት ይቻላል የመኢአድ ነበሩ። ሆኖም በአቶ ሃይሉ ሻወል ጠንካራ አና የበሰለ አመራር ምክንያት በነኛ ተቁአማት ተጠቅሞ ስልጣን የመያዝ አላማው አልሳካ ሲለው ጊዜ ድሮም ጀምሮት የነበረወን የአፍራሽ አና ወያንያው ተልዕኮ አፋፍሞ በመቀጠል ቅንጅትን በማፍረሱ ስራ ግንባር ቀደም ሚና ተጫወተ።
ሌላው ደግሞ የክህደት ስራ ባልደረባው በነበረው አቶ ልደቱ አያሌው አና በሌሎችም ተገልጾ አንደነበረው ብርሃኑ ቅንጅትን ማፍረስ የጀመረው 97ቱ ምርቻ ሳየካሄድ በፊት ነበር። ያም ከምርቻ ቦርድ አና ወያኔ ጋር ከቅንጅት አመራሮችና አባላት ጀርባ በመደራደር ቅንጅትን ለተሸናፊነት ማዘጋጀት ነበር። ደግሞም ብርሃኑ አና ፀረ አማራ ግብራበሮቹ አንዲሁም ወያኔ አለቆቹ ቅንጅት ስልጣን ላይ ከወጣ አማራ ስልጣን ላይ ወጣ ወይም ይወጣል የሚል ጠንካራ እምነት ነበራቸው። ያንን አምነቱን ነው ብርሃኑ ባንድ መድረክ ላይ አምልጦት የተናገረው። የትግሬውን አምባገነን አውርጄ የአማራውን አምባገነን ለመተካት አይደለም የምታገለው ብሎ ነበር። ያን ባለበት አፉ ነው አሁን ደግሞ በጎንደርና በጎጃም የአማራውን ተጋድሎ አየመርሁ ነኝ የሚለን። ግን አያረገ ያለው ከወያኔ ጋር በመቀናጀት የሚጠሉትን አማራን በአያውቀው ግንቦት 7 ሰበብ አያስፈውጀው ነው። ብርሃኑ ከስርቤት ስለቀቅ በወያኔ የተሰጠውን ሚሽን ለመወጣት መሽቶ ሳይነጋ ነው ወደ አዉሮፓ ከዚአም አሜሪካ የኮበለለው። የይስሙላ እስር ቤት ሆኖ በጎበዝ አለቆቹ በአንዳርጋቸው ጽጌ እና ብርሃነ መዋ ሲያስፈጽም የነበረውን በአውሮፓ አና ሰሜን አሜርካ የነበሩ ቻፕተሮች ሙሉ በሙሉ መጥፋታቸውን አና የዲያስፖራው አንድነት መፍረሱን ካረጋገጠ በሁዋላ የላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ማጭበርበሪያ እና ህዝቡን ከእውነተኛው ትግሉ ማዘናግያና ወያኔን በስልጣን ማቆያ ስራውን ቀጥሎ እስካሁን ይገኛል። ብርሃኑ ድሮም ወያኔ ነው አሁንም ወያኔ ነው። ችግሩ ብርሃኑ ሲበዛ ስልጣን የጠማው ሰው ስለሆነ በወያንያዊ ሚሽኑ ጀርባ ዎያኔን አራሷን አና ተቃዋሚ ውስጥ ያሉ ቡድኖችን አታሎ አና ተጠቅሞ ስልጣን መያዝ ይፈልጋል። በዚያ መካከል ለዚህ አላማዬ መሰናክል ይሆነኛል ያለው የአማራው ህብረተሰብ መጨፍጨ ፍ ይቀጥላል ማለት ነው። ቸር ይግጠመን።