Wednesday, February 21, 2018

ኢትዮጵያ ላለችበት ችግር መውጫ መፍትሄ ምክር ለኢሕአዴግ

       ከ ሁለት ዓመት የበለጠን የህዝብ ጫናን ተከትሎ ኢህአዴግ የታወቁ የፖለቲካ አስረኞቺን ለቀኩ ብሎአል የተቀሩ ቢኖሩም ቅሉ። ከተቀሩት ታዋቂ የፖለቲካ አስረኞች ዉስጥ የዋልድባ መነኮሴዎችና በሐሰት የግንቦት 7 አባል ናቺሁ ተብለው ዘብጥያ የተወረወሩት አነ ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና አብረዋቸው የተከሰሱት የጦር መኮንኖች ይገኙበታል። ይሄ ታዲያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣትና ሌሎች የፖለቲካ አስረኞችን አያካትትም። ኢህአዴግ ይሄን ልያደርግ የቻለው ይሄን የተቆጣ ህዝብ ለማረጋጋት ባለው ተስፋ ነው። ሆኖም ግን ህዝቡ ላነሳው ጥያቄ የስረኞች መለቀቅ ብቻ መልስ ሊሆን አይችልም። ህዝቡ ዘረኝነት ሰለቸኝ፣ ጭቆና ሰለቸኝ፣ ድህነት ሰለቸኝ፣ ክፍፍል ሰለቸኝ ፣ አናንተ ሰለቻችሁኝ ነው እያላቸው ያለው። ሆኖም ግን ኢህአዴግ ለነኚህ የህዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ በፊት አርጎት የነበረውን ግዜአዊ አዋጅ አውጆአል። እነኚህ አጉል ድርጊቶቹ ደግሞ ይሄን ለለውጥ የተነሳ ህዝብ የፈለገውን ለውጥ ከማግኘት አያቆመውም። ይልቁን በፍትሄው ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተደራድሮ ግዘአው የሽግግር መንግስት መመስረት ብቻ ነው።
           ይሄ ኢህአዴግ አገዛዝ ሊረዳው ያልቻለው ነገር ቢኖር ሀገርን በጊዜአዊ አዋጅ ማስተዳደር ዘላቂነት አንደሌለው ነው። ሆኖም ግን ይሄን ሳይረዱት ቀርተው አይደለም። ሆኖም ግን ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ይህቺን ደሃ አገር ከ27 ዓመት ባላነሰ ሀብቷን ሲመዘብሩ አና ይባስ ህዝቡን ሲያደህዩ ኖረው ይሄ የህዝብ መአበል ድንገተኛና ከህዝብ የዘረፉትን ሀብት የማሸሽያ ግዜ የማይሰጥ ሆኖ ስላገኙት ነው። ያለአግባብ ያካበቱትን ንብረት አስክሸጡና ገንዘቡን አስክያሸሹ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት ባለፉት አመታት ወደ ውጪ ሃገራት ባንኮች ካሸሹአቸው ገንዘቦች በተጨማሪ ማለት ነው። ከዚያም በተጨማሪ ይሄ የህዝብ አመጽ አስከነ ነብሳቺን ይውጠናል በሚለው ፍራቻቸው ነው። ሌላውና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በጠመንጃ ኃይል አንጂ በሰላማዊ የሕዝብ ትግል ወደ ስልጣን ባለመምጣታቸው ነው። በኃይል መጥቻለሁና ከፈለጋችሁ በኃይል አውርዱኝ ነው ነገሩ።
            ይሄ አካሄዳቸው ደግሞ የአጥፍቶ ጥፋ አካሄድ ነው። እኔ ካልኖርኩ ሰርዶ አይብቀል ነው። ሀገሪቷ ወደ አላስፈላጊ የርስ በርስ ትልልቅ እንድትገባ ካላቸው ደንታ ቢስነት የተነሣ ነው። ሆኖም ግን በኔ ግምት እነሱ ወደዱም ጠሉም በህዝብ ኃይል ከስልጣን ይወርዳሉ እንጂ አነሱ ያሰቡት የርስ በርስ ትልልቅ በፍጹም አይካሄድም። ለዚያም ብዙ ምክንያቶች አሉ። በመጀመርያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስልጡን ሕዝብ ነው። ይሄም ስልጡንነቱ በቅኝ ያልተገዛ ሕዝብ በመሆኑ ነው። ስልጡንነቱንም በ1997ቱ ምርጫ ግዜ በነቂስ ወጥቶ የኢህአዴግ ሽፍጦች ሳይበግሩት በግዜው አግኝቶት በነበረው ግዘአዊ የዴሞክራሲ ተሞክሮ ተጠቅሞ ድምጹን በመስጠት ነው። ሌላው መክንያት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈርያ እግዚአብሔር ያለው ሕዝብ ነው። በሰው ስቃይና አልቂት አያምንም። የዚህ አይነት አምነት የሌላቸው በስልጣን ላይ ያሉት የኢህአዴግ መሪዎች ብቻ ናቸው። ከዚያ በተጨማሪ ህዝቡ ባሁኑ ሰዓት በጋራ አየታገለ መሆኑ ነው። ይሄ ደግሞ የሚአሳየው ኢህአዴግ ለ27 ዓመት የቀመረው የዘር መከፋፈል ድርጊት አንዳልሰራ ነው። በመጨረሻም ይሄ በአሁን ሰዓት የኢህአዴግን የአንባገነን በትር ተቅዋቁሞ ለውጥ አያሻ ያለው ወጣት አንደ ተማሪው ንቅናቄ ዘመን በጣም የነቃ መሆኑ ነው።
            ሰለዚህ በዚህ ግዜ ብቸኛ አማራጭ የሚሆነው የህዝብ ድጋፍ ካላቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ገለልተኛ ታዛቢና አደራዳሪ ባለበት ድርድር አካሂዶ ግዜአው የሽግግር መንግስት መመስረት ብቻ ነው። ይሄ የሽግግር መንግስትም ሊቆይ የሚችለው ፓርቲዎች የምርጫ ዘግጅትና የምረጡኝ ቅስቀሳ አድርገው ሕዝብ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የመረጠው መንግስት ሲመጣ ብቻ ነው። ያደግሞ ባገሪቷ አይነተኛ የሆነ የሰላምያዊ መንግስት ልውውጥ አንድመጣ ያደርጋል። ያን ማድረግ ደግሞ በታሪክ የምአስመሰግን ስልጡን ተግባር ነው ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቺግሩን በራሱ ዉይይትና ምቻቻል መፍታቱን ያሳያል። ኢህአዴግም የኢትዮጵያ ህዝብም አላስፍላጊ ከሆነ የለውጥ ዉጤት ይድናል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ወጣት አልአዛር ታምር