Wednesday, July 4, 2018

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዶክተር አብይን ጥሪ አክብረው ኢትዮጵያ ይግቡ። ምክንያት አይደርድሩ።

ከአንድ የግንቦት ሰባት ደጋፊ ከሆነ በኔ እድሜ አካባቢ ያለ ወጣት ልጅ ጋር እንደድንገት እስታርባክስ (Starbucks) ተብሎ በሚጠራው ብቸኛው የግንቦት ሰባት የጦር ቀጠና ተገኝቼ ስወያይ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የአንቀጽ 39 ደጋፊና የወያኔን ከፋፋይ ህገ መንግስት አርቃቂ ነው ስለው አይ እሱ ጥሩ አስተማሪዬ ነበረ አለኝ። ጥሩ አስተማሪነቱ አገርን በቀና ለመምራት ብቁነት ጋር ምን ያገናኘዋል ስለው መልስ አጣ። ከዝያ ቀጥዬ ይሄ የጦር ትግል አካሂዳለው የሚለውም አጭበርባሪ ቀጣፊ ነው ብዬ ስጀምር ማነው እሱ ብሎ እንደ አውራ ዶሮ አቆበቆበ። ፕሮፌሰር ጀነራል ብርሃኑ ነዋ ሰለው እንደ ፌንጣ መዝለል ጀመረ። ፈስ ያለበት ዝላይ አይወድም አሉ። በመቀጠልም እሱ ባክህ አንድ ወታደር አንኩዋን የለውም። ግንቦት 7 የሚባልም የለም አልኩት። እሱም ሲመልስ አንተ ልደቱን በየነን አሁን ደግሞ ብርሃኑን ትቃወማለህ ታድያ መሪ ከሰማይ ላይ ይውረድልህ እንዴ ብሎኝ ነበር። ግንቦተዎች እንዲህ የሚሉት አዋዜ ነበራቸው። ይሀው እነሆ የጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የ27 ዓመት ምርር ያለ ጸሎት Dr አብይን ከሰማይ ላይ አወረደልን።
ታድያ እሳቸው በቅርብ ግዜ ባደረጉትና ብዙዎችን ባስደመመ የፓርላማ ንግግራቸው ላይ ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደሀገሮ ገብተው በሰላም የፖለቲካው ሂደት ተካፋይ ይሁኑ ብለው ጥሪ አቅርበውለታል። ሆኖም ግን Dr አብይ እንደ ቀድሞ መረጃ ባለሙያነታቸው ፕሮፌሰር ጀነራል ብርሃኑ አንዳች ወታደርም ሆነ እውነተኛና እሱ ልያስመስል እንደሚሞክረው ሀገር ዉስጥ በህቡህ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አንደሌለው በሚገባ ያውቃሉ። ደግሞም ብያንስ ብያንስ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ስለግንቦት 7 የሚያውቀውን ሁሉ ለመርማሪዎቹ ሳይዋሽ እንደተናገረው ሁሉ ለDr አብይም ከስር ቤት ተፈቶ ለሰአታት ሲወያዩ እንደነገራቸው አልጠራጠርም። ግንቦት 7 በትጥቅ ተዋጊም ሆነ በህቡህ ተንቀሳቃሽ አባል እንደሌለው ነበር ግልፅ አድርጎ ሲናገር በቪድዮ ተላልፎ ያየነው።
ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ፕሮፌሰር ጀነራል ብርሃኑ ነጋ ከቅንጅት መሪዎች ጋራ ታስረው በተፈቱ ማግስት እንደ ዛሬዎቹ ወጣቶች ለነጻነታቸው ሲሉ የተሰው ወጣት ቤተሰቦችን ሳያፅናና በሮ ወደ አሜሪካ በተመለሰ ማግስት እዚ ያስተምራቸው የነበሩ አሜሪካዊ ተማሪዎቹን ሰብስቦ አናግሮ ነበር። ታድያ በዚያ ስብሰባ ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ ተነስቶ መቼ ነው አንተ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰህ እንደ ሌሎቹ የቅንጅት አጋሮችህ ትግሉል ምትቀጥለው? እዚህ ሸሽተህ ቀረህ እኮ ብሎ ጠይቆት ነበር። ታድያ የዛኔ በጥያቄው በግልጽ የተበሳጨውና ያፈረው የዛነው Dr ብርሃኑ ነጋ እንደ መንግስቱ ሃይለማርያም ተረቤዛውን መደለቁን እና እንደ መለስ ዜናዊ ጠያቂውን በስም አየጠራ ማስፈራራቱንና ጥያቄን በጥያቄ መመለሱን ተያያዘው። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ፐንስልቬንያ የሚባለው የአሜሪካ ክፍለሀገር ሄጄ ተራራ ላይ እወጣለሁ ብሎ አሳወጀ። ታድያ አሁንስ ጠቅላይ ሚንስትር Dr አብይ አህመድ ያቀረቡለትን ጥር ተቀብሎ ይገባ ይሆን?
መልሴ አይገባም ነው። በቅንጅት ግዜ እንዲመለስ ተጠይቆ ያልተመለሰው በግንቦት 7 1997 ምርጫ እለት የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጹን በመስጠት ወያኔን ያሸነፈበትን ድሉን ድርጅታዊ አሻጥር በመሥራት እንዳስቀማ ህዝቡ ስላወቀ ነው። እሱና ልደቱ ቅንጅት ውስጥ ሰርገው የገቡ የወያኔ አሻጥረኞች ነበሩ። Dr ብርሃኑ ነጋ ከዚያም አልፎ እነ ሽብሬ ደሳለኝና ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በወያኔ ጥይት ከተሰዉ በሁዋላ ተቃዋሚዎች ጠርተወት የነበረውንና ወያኔን አርበድብዶ የነበረውን ለሶስት ቀናት ቤት ዉስጥ የመዋል አድማ ማናቸውንም የቅንጅት አመራሮች ሳያማክር በራሱ ፈቃድ ከDr በየነ ጴጥሮስ ጋር በመሆን በወያኔ ቴሌቭዥን ላይ ወጥቶ ያድማውን ጥሪ ሰርዘናል  በማለት አድማው እንዲቀርና ወያኔም አፎይ በማለት ወድያውኑ አዋጅ በማወጅና በሌሎች ዘዴዎች ተጠቅሞ ስልጣኑን ሊያጠናክር ችሏል። ነገር ግን Dr ብርሃኑ የህዝብን ድምጽ ያስቀማው ገና የ97 ምርጫ ሳይካሄድ ነበር። ምርጫው እየተቃረበ በነበረበት ሰዓት የምርጫ ሂደት ድርድር ሲካሄድ ቅንጅት ወክሎት ይደራደር የነበረ እሱ ነበር። 

Wednesday, February 21, 2018

ኢትዮጵያ ላለችበት ችግር መውጫ መፍትሄ ምክር ለኢሕአዴግ

       ከ ሁለት ዓመት የበለጠን የህዝብ ጫናን ተከትሎ ኢህአዴግ የታወቁ የፖለቲካ አስረኞቺን ለቀኩ ብሎአል የተቀሩ ቢኖሩም ቅሉ። ከተቀሩት ታዋቂ የፖለቲካ አስረኞች ዉስጥ የዋልድባ መነኮሴዎችና በሐሰት የግንቦት 7 አባል ናቺሁ ተብለው ዘብጥያ የተወረወሩት አነ ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና አብረዋቸው የተከሰሱት የጦር መኮንኖች ይገኙበታል። ይሄ ታዲያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣትና ሌሎች የፖለቲካ አስረኞችን አያካትትም። ኢህአዴግ ይሄን ልያደርግ የቻለው ይሄን የተቆጣ ህዝብ ለማረጋጋት ባለው ተስፋ ነው። ሆኖም ግን ህዝቡ ላነሳው ጥያቄ የስረኞች መለቀቅ ብቻ መልስ ሊሆን አይችልም። ህዝቡ ዘረኝነት ሰለቸኝ፣ ጭቆና ሰለቸኝ፣ ድህነት ሰለቸኝ፣ ክፍፍል ሰለቸኝ ፣ አናንተ ሰለቻችሁኝ ነው እያላቸው ያለው። ሆኖም ግን ኢህአዴግ ለነኚህ የህዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ በፊት አርጎት የነበረውን ግዜአዊ አዋጅ አውጆአል። እነኚህ አጉል ድርጊቶቹ ደግሞ ይሄን ለለውጥ የተነሳ ህዝብ የፈለገውን ለውጥ ከማግኘት አያቆመውም። ይልቁን በፍትሄው ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተደራድሮ ግዘአው የሽግግር መንግስት መመስረት ብቻ ነው።
           ይሄ ኢህአዴግ አገዛዝ ሊረዳው ያልቻለው ነገር ቢኖር ሀገርን በጊዜአዊ አዋጅ ማስተዳደር ዘላቂነት አንደሌለው ነው። ሆኖም ግን ይሄን ሳይረዱት ቀርተው አይደለም። ሆኖም ግን ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ይህቺን ደሃ አገር ከ27 ዓመት ባላነሰ ሀብቷን ሲመዘብሩ አና ይባስ ህዝቡን ሲያደህዩ ኖረው ይሄ የህዝብ መአበል ድንገተኛና ከህዝብ የዘረፉትን ሀብት የማሸሽያ ግዜ የማይሰጥ ሆኖ ስላገኙት ነው። ያለአግባብ ያካበቱትን ንብረት አስክሸጡና ገንዘቡን አስክያሸሹ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት ባለፉት አመታት ወደ ውጪ ሃገራት ባንኮች ካሸሹአቸው ገንዘቦች በተጨማሪ ማለት ነው። ከዚያም በተጨማሪ ይሄ የህዝብ አመጽ አስከነ ነብሳቺን ይውጠናል በሚለው ፍራቻቸው ነው። ሌላውና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በጠመንጃ ኃይል አንጂ በሰላማዊ የሕዝብ ትግል ወደ ስልጣን ባለመምጣታቸው ነው። በኃይል መጥቻለሁና ከፈለጋችሁ በኃይል አውርዱኝ ነው ነገሩ።
            ይሄ አካሄዳቸው ደግሞ የአጥፍቶ ጥፋ አካሄድ ነው። እኔ ካልኖርኩ ሰርዶ አይብቀል ነው። ሀገሪቷ ወደ አላስፈላጊ የርስ በርስ ትልልቅ እንድትገባ ካላቸው ደንታ ቢስነት የተነሣ ነው። ሆኖም ግን በኔ ግምት እነሱ ወደዱም ጠሉም በህዝብ ኃይል ከስልጣን ይወርዳሉ እንጂ አነሱ ያሰቡት የርስ በርስ ትልልቅ በፍጹም አይካሄድም። ለዚያም ብዙ ምክንያቶች አሉ። በመጀመርያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስልጡን ሕዝብ ነው። ይሄም ስልጡንነቱ በቅኝ ያልተገዛ ሕዝብ በመሆኑ ነው። ስልጡንነቱንም በ1997ቱ ምርጫ ግዜ በነቂስ ወጥቶ የኢህአዴግ ሽፍጦች ሳይበግሩት በግዜው አግኝቶት በነበረው ግዘአዊ የዴሞክራሲ ተሞክሮ ተጠቅሞ ድምጹን በመስጠት ነው። ሌላው መክንያት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈርያ እግዚአብሔር ያለው ሕዝብ ነው። በሰው ስቃይና አልቂት አያምንም። የዚህ አይነት አምነት የሌላቸው በስልጣን ላይ ያሉት የኢህአዴግ መሪዎች ብቻ ናቸው። ከዚያ በተጨማሪ ህዝቡ ባሁኑ ሰዓት በጋራ አየታገለ መሆኑ ነው። ይሄ ደግሞ የሚአሳየው ኢህአዴግ ለ27 ዓመት የቀመረው የዘር መከፋፈል ድርጊት አንዳልሰራ ነው። በመጨረሻም ይሄ በአሁን ሰዓት የኢህአዴግን የአንባገነን በትር ተቅዋቁሞ ለውጥ አያሻ ያለው ወጣት አንደ ተማሪው ንቅናቄ ዘመን በጣም የነቃ መሆኑ ነው።
            ሰለዚህ በዚህ ግዜ ብቸኛ አማራጭ የሚሆነው የህዝብ ድጋፍ ካላቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ገለልተኛ ታዛቢና አደራዳሪ ባለበት ድርድር አካሂዶ ግዜአው የሽግግር መንግስት መመስረት ብቻ ነው። ይሄ የሽግግር መንግስትም ሊቆይ የሚችለው ፓርቲዎች የምርጫ ዘግጅትና የምረጡኝ ቅስቀሳ አድርገው ሕዝብ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የመረጠው መንግስት ሲመጣ ብቻ ነው። ያደግሞ ባገሪቷ አይነተኛ የሆነ የሰላምያዊ መንግስት ልውውጥ አንድመጣ ያደርጋል። ያን ማድረግ ደግሞ በታሪክ የምአስመሰግን ስልጡን ተግባር ነው ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቺግሩን በራሱ ዉይይትና ምቻቻል መፍታቱን ያሳያል። ኢህአዴግም የኢትዮጵያ ህዝብም አላስፍላጊ ከሆነ የለውጥ ዉጤት ይድናል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ወጣት አልአዛር ታምር